የአዲስ ከተማ ክፍለተማ ትምህርት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በክፍለከተማው ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አይሲቲ መምህራን ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናው በዋናነት የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶች አጠቃቀም ና አያያዝ ላይ ያተኮረ ሲሆን ብልሽት ሲያጋጥምም እንዴት መጠገን እንደሚቻል በተግባር የተደገፈ መሆኑ እስካሁን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችልና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹና ተስማሚ አካባቢ መፍጠር የሚያስችል መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ እንዳስታወቁት የስኩል ኔት መሰረተ ልማትን በአግባቡ መያዝና መጠበቅ ከተቻለ እንዲሁም ወቅቱን የጠበቀ ጥገና እየተደረገለት መሄድ ቢችል በአሁን ሰዓት እየወጣ ያለውን አላስፈላጊ ወጪ መቀነስና የሃገርን ሃብት መጠበቅ እንደሚቻል ጠቁመው ክፍለከተማው እንዲአይነት ስራን ለመስራት መነሳሳቱን በማድነቅ ሌሎችም ክፍለከተማዎች ይህንን ተሞክሮ ሊወስዱ እንደሚገባ ጠቁመው ትምህርት ቢሮው ወደፊትም ከክፍለከተማው ጋር በጋራ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry