ቀን 12 / 3/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከመምህራን ጋር ውይይት አካሄደ።

በውውይቱ በአስራ አንዱ ክፍለከተሞች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ2,500 በላይ የሚሆኑ መምህራን እንዲሁም የቢሮው እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ባደረጉት ገለጻ ውይይቱ ከመምህራን ጋር ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታ መሰረት በማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ፈጥሮ አሁን የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ መቀልበስ እንዲቻል ለማድረግ እንደሚረዳ አስታውቀዋል።

ኃላፊው አክለውም መምህራን በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቁመው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ በአሸባሪው ህውሀትና ለዚህ ቡድን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ የሚገኙ የውጭ ሀይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ መምህራን ማህበረሰቡን ከማንቃት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ መምህራን ከመድረኩ በቢሮ ኃላፊው የቀረበውን የመወያያ ሰነድ መሰረት አድርገው የተለያዩ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በዋናነትም መምህራኑ ሀገራችን የገጠማትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚደረጉ የተለያዩ ተግባራት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው በየትምህርት ቤቶቻቸውም ከተማሪ ወላጆች ጋር በጋራ በመሆን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እንዲኖር የሚጠበቅባቸውን ተግባር ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የመድረኩም የአቋም መግለጫ በመምህር ታረቀኝ ወልደሃና ቀርቦ የመድረኩ ማጠቃለያ ሆናል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry