ቀን 9 / 3/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አደረገ፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ሀገራችን አሁን የገጠማትን ችግር ለማለፍ እንድትችል የትምህርት ማህበረሰቡ በተለይም ደግሞ መምህራን የሚኖራቸዉ ሚና የጎላ መሆኑን በመጥቀስ ሀገርን ማፍረስ ዋና አላማዉ አድርጎ የተነሳዉን የጥፋት ሀይልን በተደራጀ አቅም ለመመከት እንዲቻል የከተማዉ መምህራን ማህበር በየደረጃዉ መስል ውይይቶችን በማድረግ የትምህርት ልማት ስራዉ ውጤታማ እንዲሆን እና መንግስት የጀመረዉ ህግን የማስከበር ተግባር ከዳር እንዲደርስ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ የገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸዉ ሀገርን መሰረት ያደረጉ እንዲሁም በትምህርት ተቋማት ላይ የሚከናወኑ ጉዳዮች ሁላ ማህበሩን መለከቱታል ያሉ ሲሆን ሰላማዊ መማር ማስተማር እንዲረጋገጥ ሚናችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ድንቃለም አክለዉም ቀደም ሲል በማህበሩ የተጀመረዉ የደም ልገሳ በተጠናከረ ደረጃ እንዲቀጥል እና ለተፈናቃይ ወገኖች በሚደረገዉ ድጋፍ ላይ የበኩላችንን አስተዋጽዎ ልናደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry