ቀን 7/3/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት እና የመቶ ቀን እቅድ የጥቅምት ወር አፈፃፀም ዙሪያ ከቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ ::

በውይይት መድረኩ በ2014 ዓ.ም በትምህርት ልማት ዘርፍ ሊከናወኑ ከታቀዱ እቅዶች ውስጥ የበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የመቶ ቀናት እቅድ የጥቅምት ወር አፈፃፀም ሪፖርቶች እንዲሁም ከፕላን ኮሚሽን ለቢሮ የተሰጡ ግብረ መልሶች በቢሮው እቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ::

በመድረኩ ተሳታፊዎች በሪፖርቱ ቢካተቱ እና ትኩረት ቢሰጥባቸዉ እንዲሁም ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸዉን ሃሳቦችና ጥያቄዎች አቅርበዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ሪፖርቱ የቀረበበትን አግባብ አድንቀው ሪፖርቱን ሊያዳብሩ የሚችሉ ከሰራተኞች የተነሱ ነጥቦች በሪፖርቱ ሊካቱ ይገባል ብለዋል ::

የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው የእቅድና ሪፖርቶች መጣጣም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተው ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

“እኔም የሰፈሬ ፖሊስ እና የሰላም ዘብ ነኝ”

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry