ቀን 7 / 3/ 2014 ዓ.ም

በሰላማዊ መማር ማስተማርና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር ተደረገ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች፤ የአስተዳደር ተወካዮች፣ሱፐርቫይዘሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ምክክር ተደርጓል።

የምክክሩ ትኩረት በሀገራችን ባለው ወቅታዊ ጉዳይ ፤ በተማሪ ስነ ምግባር ፤ በሰላማዊ መማር ማስተማር እንዲሁም በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሆን በሰነድ ቀርቦ የጋራ ግንዛቤ ተይዞበታል።

በምክክሩ ላይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ የግል የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ኃላፊነት በመወጣት ለሀገራቸው አስተዋፅኦ በማበርከት ከሌላው ጊዜ በተለየ ከመንግሥት ጋር ተባብረው በመስራት፤ የውስጥና የውጭውን አደጋ ለመመከት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። አቶ አደፍርስ አክለውም የኢትዮጵያ ብልጽግና ያልተዋጠላቸው ኃይሎች በግል ትምህርት ተቋማት አላማቸውን ለማሳካት እንዳይሞክሩ ሰላማዊ መማር ማስተማር ተጠናክሮ እንዲቀጥል መስራት አለበት ብለዋል።

“እኔም የሰፈሬ ፖሊስ እና የሰላም ዘብ ነኝ”

ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry