ቀን 2 / 3/ 2014 ዓ.ም

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቅን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን በተሰሩ ጠንካራ ስራዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናዉ በሰላም በዛሬዉ ዕለት መጠናቀቁን ሀላፊዉ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ደረጃ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት ሀላፊዉ በፈተና ሂደቱ ከትምህርት ቢሮ እስከ ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ድረስ ፈተናውን እንዲመሩ እና እንዲያስተባብሩ የተደለደሉ ፈታኞች ፣ ሱፕር ቫይዘሮች ፣የጣቢያ ኃላፊዎች በተለይም ደግሞ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፣ ተማሪዎች እና ወላጆች የተሰጣቸዉን ሀላፊነት በትጋት በመፈጸማቸዉ ለተገኘዉ ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የቢሮ ሀላፊዉ አክለዉም ፈተናዉ ሰላማዊ ሆኖ ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ሳደርጉ ለነበሩ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ለፖሊስ መዋቅሩ አባላት ለነበራቸዉ የነቃ ተሳትፉ ላቅ ያለ ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry