ቀን 2 / 3/ 2014 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተሳታፊዎች በፈተናው ማጠናቀቂያ ለተፈናቃዩች ድጋፍ አደረጉ።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ ተፈታኝ የነበሩ ተማሪዎች በፈተናው ማጠናቀቂያ ለተፈናቃዩች ድጋፍ አደረጉ።

የክ/ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር ልገሳውን ያደረጉት አስተባባሪዎች፣ ሱፐርቫዘሮች፣ፈታኞችና ተማሪዎች መሆናቸውን ገለፀው፤ በራሳቸው ተነሳሽነት ግምቱ 75 ሺ ብር የሚያወጣ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ሀላፊው ለተደረገው ድጋፍ በራሳቸውና በትምህርት ፅ/ቤት ስም ምስጋና ማቅረባቸዉን እንዲሁም በአራዳ ክፍለ ከተማ በ6 የፈተና ጣቢያዎች ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን መግለጻቸዉን ከአራዳ ከፍለ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry