ቀን 2 / 3/ 2014 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው በዛሬው ዕለት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።

ተማሪዎቹ ደማቸዉን ፣ የተለያዩ የምግብ አይነቶችንና አልባሳቶችን የለገሱ ሲሆን በዋናነትም ከለገሷቸው የምግብ አይነቶች መካከል ፓስታና ሩዝ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደመውሰዳቸው ዩኒፎርማቸውን ከመስጠታቸው ባሻገር ደብተሮችንም አበርክተዋል።

ተማሪዎቹ ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ከግንዛቤ አስገብተው በራሳቸው ተነሳሽነት ይህንን የመሰለ የበጎ ፍቃድ ስራ መስራታቸው ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን ተግባር በመሆኑ ከፍተኛ ምስጋና እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ ገልጸዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry