ቀን 2 / 3/ 2014 ዓ.ም

ከጥቅምት 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

በከተማ አስተዳደሩ ፈተናው ከጥቅምት 29/2014 ዓ.ም እስከ ህዳር 2/2014 ዓ.ም ድረስ በ62 የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቶ ያለ ምንም እንከን መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።

አቶ ዲናኦል አክለውም በአዲስ አበባ 36,401 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው 35,844 ተማሪዎች መፈተናቸውን ገልጸው በተጨማሪም ከሰሜንና ከደቡብ ወሎ ዞኖች ባለው ወቅታዊ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ 122 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ አበባ በ62 የፈተና ጣቢያዎች 970 ፈታኞች፣312 ሱፐርቫይዘሮች፣62 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣62 አስተባባሪዎችና 600 የፖሊስ አባላት በፈተናው ሂደት ተሳታፊ መሆናቸውን አቶ ዲናኦል ገልጸው ፈተናው ያለምንም እንከን ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry