ቀን 2 / 3/ 2014 ዓ.ም

ከጥቅምት 29/2014ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

በክፍለ ከተማው የነበረውን የፈተና ሂደት አስመልክቶ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ በሰጡት አስተያየት ፈተናው በክፍለ ከተማው በሚገኙ 4 የፈተና ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁንና በዚህም የኮማንድ ፖስት አባላትን ጨምሮ የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸው የፈተና ስርአቱ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን አስረድተዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በክፍለ ከተማው 1717 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸው በፈተና ጣቢያዎቹ 44 ፈታኞችና 13 ሱፐር ቫይዘሮችን ጨምሮ 85 ፖሊሶች እና የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት አባላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን አስታውቀዋል።

በክፍለ ከተማው የፈተና ስርአቱ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በፈተና ጣቢያዎቹ ድጋፍና ክትትል ሲያደርጉ ያገኘናቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ አቶ ስዩም መኮንን እና የክፍለ ከተማው የወላጅ ማህበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ኤልሳቤት ብርሀኑ በሰጡት አስተያየት ማህበራቸው ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸው የኮማንድ ፖስት አባል እንደመሆናቸው ፈተናው እስኪጠናቀቅ በየጣቢያዎቹ በመዘዋወር ክትትል ማድረጋቸውን አስረድተዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry