ቀን 30 /2/ 2014 ዓ.ም

በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በ62 የፈተና ጣቢያዎች የተጀመረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በዛሬው ዕለትም እንደቀጠለ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ አደፍርስ ኮራ ጋር በመሆን ከፍተኛ 23 እና ዕውቀት ለህብረት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የፈተናውን ሂደት ተመልክተዋል።

ከፍተኛ 23 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኘው የፈተና ጣቢያ ከአንድ የመንግስትና ከሁለት የግል ትምህርት ቤት የመጡ 1096 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙና 28 ፈታኞችን ጨምሮ 8 ሱፐር ቫይዘሮች ተመድበው በስራ ላይ እንደሚገኙ የፈተና ጣቢያው ኃላፊ አቶ መስፍን መኩሪያ ገልጸዋል።

ዕውቀት ለህብረት ትምህርት ቤት በሚገኘው የፈተና ጣቢያ 1037 የሶስት የግል ትምህርት ተማሪዎች በፈተና ላይ የሚገኙ ሲሆን በጣቢያውም 26 ፈታኞችና 6 ሱፐር ቫይዘሮችን ጨምሮ ሌሎች የፈተና አስተባባሪዎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ከፈተና ጣቢያው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደጃች ባልቻ አባነብሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዕውቀት ለፍሬ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የፈተናውን ሂደት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በፈተና ጣቢያዎቹ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተሰጠ እንደሚገኝ የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል።

ሀላፊዎቹ ምልከታ ባደረጉባቸዉ የመፈተኛ ጣቢያዎች ላይ ፈተናቸዉን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎችንም አበረታተዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry