ቀን 29 /2/ 2014 ዓ.ም

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 62 የፈተና ጣቢያዎች ለ36,401 ተማሪዎች በዛሬው እለት መሰጠት ጀምራል፡፡

ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንዱ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ኮከበ ጽባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን በፈተና ጣቢያው ፈተናው ያለምንም እንከን መጀመሩን ተመልክተናል።

በጣቢያው የኮከበ ጽባህን ጨምሮ የማግኔት ትምህርት ቤትና በግላቸው የሚፈተኑ 744 ተማሪዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ እና 22 ፈታኞችና 6 ሱፐርቫይዘሮች ተመድበው በስራ ላይ መሆናቸውን ከፈተና ጣቢያው ኃላፊ ከአቶ መለሰ ይልማ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በጠዋቱ የመፈተኛ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የእንግሊዝኛ ፈተና መሰጠት የጀመረ ሲሆን ተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንዲሁም ፈተናችሁን በፍፁም መረጋጋት እና ስነ- ምግባር በተሞላበት መልኩ እንድትፈተኑ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry