ቀን 29 /2/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እና ምክትል ቢሮ ሀላፊዉ አቶ አድማሱ ደቻሳ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባለዉ ችግር ምክንያት ተፈናቅለዉ የ12ኛ ክፍል ፈተና አዲስ አበባ በመፈተን ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በፈተና ጣቢያ ተገኝተዉ አበረታቱ፡፡

ተፈታኞቹ ከሰሜን እና ደቡብ ዞኖች እንዲሁም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከሪያድና ጅዳ የመጡ ሲሆኑ 148 ተማሪዎች ፈተናዉን ለመውስድ ተመዝግበዉ 125 ተማሪዎች መፈተናቸዉን ከፈተና ጣቢያዉ የተገኘዉ መረጃ ያሳያል፡፡

በደግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ቤት ተገኝተዉ ተፈታኞችን ያበረታቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ተማሪዎች አሁን ያጋጠማቸዉ ችግር ስያረብሻቸዉ ፈተናዉን በተረጋጋ ስሜት መፈተን እንደሚገባቸዉ እንዲሁም ቢሮዉ ተፈታኞችን በማንኛዉም ሁኔታ ለመርዳት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተማሪዎቹ ፈተናዉን ተፈትነዉ እስኪጨርሱ ድረስ ምሳቸዉን ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘዉ ክብብ በነጻ እንዲመገቡ የተደረገ ሲሆን በከሰሃቱ የፈተና ጊዜ ተፈታኞች የሂሳብ ትምህርትን ፈተና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry