ቀን 29 /2/ 2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በ62 የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በዛሬው ዕለት ተጀመረ።

ፈተናው ከሚሰጥባቸው 62 ጣቢያዎች መካከል ኮከበ ጽበሀ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እቴጌ መነን የልጅ አገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስተር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ተገ ኝተው የፈተናውን ሂደት ተመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የፈተና ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት በአዲስ አበባ ደረጃ በ62 የፈተና ጣቢያዎች 36,401 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ተማሪዎቹም ፈተናውን ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በመፈተን ላይ እንደሚገኙ መመልከታቸውን ገልጸው የፀጥታ አካላትም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጣቸውን በመጥቀስ ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎችም መልካም ውጤት እንዲገጥማቸውና ቀጣዩ የህይወት ምዕራፋቸው ስኬታማ እንዲሆን ተመኝተዋል።

የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በበኩላቸው በመላ ሀገሪቱ 617,000 ተማሪዎች ለመፈተን መመዝገባቸውንና ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል 91.5% የሚሆኑት በዛሬው ዕለት ፈተናውን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ፈተናውን በተለያዩ ምክንያቶች ያልወሰዱ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ እንዲፈተኑ እንደሚደረግ በመጥቀስ ሀገሪቱ በዚህ አይነት የፀጥታ ችግር ውስጥ ሆና ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መካሄድ መጀመሩ ጠንካራ ሀገር መሆኗን እንደሚያሳይ አስገንዝበዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry