ቀን 25 /2/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች በሀገራዊ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች እና አመራሮች ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን አደጋ በተመለከተ በዛሬዉ እለት ውይይት አድርገዋል፡፡ በመድረኩ የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ሲሆኑ ሀገራችን የገጠማትን አደጋ ለመቀልበስ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ በበኩላቸዉ ሀገራችን የገጠማትን ችግር በልጆቻ ክንድ እንደምትወጣዉ ገልጸዉ ይህንን በተመለከተም በአስቸካይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ጉዳዮች ውጤታማ እንዲሆኑ ሁላችንም የሚናችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ አንድነታችንን በማጠናከር ለጋራ ጠላታችን በተደራጀ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ተገቢዉን መረጃ ከተገቢዉ የመረጃ ምንጭ ማግኘት ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰራተኞችም በበኩላቸዉ ሀገርን ለማዳን ከመንግስት ጎን የሚቆሙ መሆኑን እና የሚጠበቅባቸዉን ሁሉ አስከ መዝመት ድረስ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry