ቀን 26 /2/ 2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሀብተማርያም ከጥበቃ አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ።

ውይይቱ በዋናነት ወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደመታወጁ የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ መስራት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ገልጸው ወደ ቢሮ የሚመጡ ባለጉዳዮችም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲ ዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሀብተማርያም በበኩላቸው የጥበቃ አባላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው የቢሮው አመራሮችም ሆኑ ሰራተኞች ስራቸውን ያለምንም ችግር በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ወደ መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚመጡ ሰራተኞችም ሆኑ ባለጉዳዮች ህጋዊ መታወቂያ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው በመጥቀስ ይህ አሰራርም ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ አስረድተዋል።

የጥበቃ አባላቱም ውይይቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን በመግለጽ የተጣለባቸው ኃላፊነት ከፍተኛ እንደመሆኑ ስራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚወጡ ገልጸዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry