ቀን 22 /2/ 2014 ዓ.ም

የጀግኒት ንቅናቄ በከፍተኛ 12 ት/ቤት ተካሄደ፡፡

በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 2 ስር በሚገኘዉ ከፍተኛ 12 ት/ቤት በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ የጀግኒት ንቅናቄ ላይ የጀግኒት አምባሳደር አርቲስት ጸደንያ ገ/ማርቆስ ተገኝታለች፡፡

ንቅቅናቄው እኔም ያገባኛል፣ ይመለከተኛል አንድም ሴት በንጽህና መጠበቂያ ጉድለት ምክንያት ከት/ቤት መቅረት የለባትም! በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን የጀግኒት አምባሳደር አርቲስት ጸደንያ ገ/ማርቆስ እና ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለ200 ተማሪዎች የአበባየሽ ወይ ጥቅል አበርክተዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ ላይ በተማሪዎች ስነ-ጽሁፍ ቀርቧል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry