ቀን 18 /2/ 2014 ዓ.ም

የትምህርት አጀማርን በተመለከተ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ በተካሄደ ምልከታ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ558 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ በ2014 የትምህርት ዘመን የትምህርት አጀማመርን በተመለከተ ያካሄደዉን ምልከታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ይህወት ጉግሳ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት አቅርበዋል፡፡

የመስክ ምልከታ ሪፖርተን ያቀረቡት ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳሬክተር ሲሆኑ ምልከታዉ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል ትግበራን እና የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ ግብር ተግባራዊነትን በተመለከተ በትምህርት ቤቶች ያለዉን ዝግጅት ለማየት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ወ/ሮ ፍቅርተ በሪፖርታቸዉ አክለዉም ምልከታዉ የመማር ማስተማር ሂደት ፣ ምቹ ትምህርት ቤት መፍጠር ያለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት አመራር ያለበት እንዲሁም የህብረተሰብ ተሳትፎ ሁኔታን የቃኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በትክክለኛ ሰዓት የተካሄደ ምልከታ በመሆኑ በ2014 የትምህርት ዘመን የላቀ ስራ ለማከናወን እንደሚረዳ ገልጸዉ በምልከታዉ የቀረቡትን ጉዳዮች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በቀጣይ የጋራ በማድረግ ለውጤታማነት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ይህወት ጉግሳ በበኩላቸዉ በከተማዉ የሚሰጠዉ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን በቀጣይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry