ቀን 17 /2/ 2014 ዓ.ም

በክፍለ ከተማ ደረጃ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዉን ማጠናቀቁን አሳወቀ፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በክፍለ ከተማ ደረጃ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ በለጠ ሀይሉ ገልጸዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም በት/ቤት ሊፈጠሩ ለሚችሉ የሰላም፣ ፀጥታና የስነ-ምግባር ችግሮች እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው ያሉ ሲሆን ፈተናው ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰጥ ለሁሉም ት/ቤቶች መመሪያ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በፈተናው ሂደት ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተካሄደ መሆኑን የገለጽት አቶ በለጠ ሀይሉ በውይይቱም ከፈተና መሰረቅ ፤ ከፍተሻ፤ ከጤና አጠባበቅ፤ ከስጋት ቦታዎች እንዲሁም ከሰላምና ፀጥታ ጋር የተያያዙ ሀሳቦች መነሳታቸዉን አመላክተዋል፡፡

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 28 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 5126 ተማሪዎች በ8 የመፈተኛ ጣቢያዎች የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 /02/2014 – ህዳር 02/03/2014 ጀምሮ ለተከታታይ አራት(4) ቀናት የሚወስዱ መሆኑንም በተጨማሪ ገልጸዋል።

የክፍለው ከተማው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ፣ ፀጥታ ዘርፍ ፖሊስ አዛዥ ፣ የትምህርት ጽ/ቤት ፈተና ክፍል ፣ ጤና ፅ/ቤት ፣ መምህራን ማህበርና ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት የኮማንድ ፖስቱ አባላት መሆናቸዉን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry