ቀን 16 /2/ 2014 ዓ.ም

በትምህርት ቤቶች የመስክ ምልከታ ፕሮግራም ተካሄደ።

የመስክ ምልከታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በአቶ ዘላለም ሙላቱ የተመራ ሲሆን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት እና የስፕላሽ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ቀልቤሳ ተሳታፊ ሆነዋል ።

ገብኝቱ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ አራብሳ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ የካ አባዶ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛ እና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ ጎዴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ እድገት ጮራ እና ጋራ ጉሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ነው የተካሄደው።

የመስክ ምልከታው ወቅቱ የ2014 ዓ.ም ትምህርት የተጀመረበት እንደመሆኑ ጉብኝቱ የተካሄደባቸው ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተማሪ ተቀብለው ወደ መማር ማስተማር ስራው በመግባታቸው ተቋማቱ ያሉባቸውን ችግር ለመቅረፍ እንደሚረዳ ተጠቁሟል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ቤቶቹን በጎበኙበት ወቅት ቢሮው በትምህርት ቤቶቹ ያለውን የመምህር እጥረት ለመቅረፍ በዝውውርና በቅጥር ለማሟላት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ገልጸው በትምህርት ቤቶቹ አቅራቢያ ተጨማሪ ተማሪ ለመቀበል በመገንባት ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም በአስቸኳይ ግንባታቸው ተጠናቆ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር እንዲችሉ መስራት እንዳለባቸው ግንባታዎቹን በማካሄድ ላይ ለሚገኙ አካላት መመሪያ ሰጥተዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry