በትምህርት ጉባኤው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የወላጅ ምህበር ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በጉባኤው መክፈቻ የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ልማት ስራው በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በ2013 የትምህርት ዘመን የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን በመግለጽ ለዚህም የተማሪዎች ምገባና ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች አቅርቦት ለውጤቱ መሻሻል ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው በ2014 የትምህርት ዘመን የትምህርት ዘመንም ከተማ አስተዳደሩ ለሴክተሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዳሚቀጥል አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ትምህርት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የአዲስ ምዕራፍ ጉዞም ሆነ የብልጽግና መንገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልጸው በ2013 የትምህርት ዘመን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የፈጠረውን ተጽኖ በመቋቋም በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻል መታየቱንና ለዚህም የሁሉም ባለድርሻ አካል ተሳትፎ የላቀ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ ዘላለም አክለውም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ተዘጋጅቶ በ2014 የትምህርት ዘመን በ55 ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው በዚህ መጽሀፍ ዝግጅት ቢሮው የራሱን መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች መጠቀሙን በመግለጽ ይህ ውሳኔም ስራውን በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ማድረጉን አስገንዝበዋል።

በትምህርት ጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር እና የወላጅ ተማሪ ማህበር አመራሮች መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን የትምህርት ጉባኤው ለሁለት ቀን የሚካሄድ ሲሆን በዋናነትም የቢሮው የ2013 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2014 ዓ.ም እቅድን ጨምሮ የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና እንዲሁም አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህሩ መምሪያ ዝግጅት የደረሰበት ደረጃ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ቀንም ተቋማት ጋር የጋራ የስራ ስምምነት ሰነድ ፊርማ እንዲሁም በ2013 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry