የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በጉባኤው በክብር እንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ልማት ስራ መምህራን ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር ጋር በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በቀጣይ ጊዜያት የሙያ ማህበሩን ለመምራት በአባላቱ የሚመረጡ አመራሮች የመምህርነትን ሙያ በማክበር የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚጠበቅባቸው በመጥቀስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከማህበሩ ጋር አብሮ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ የሙያ ማህበሩን የ2013ዓ.ም ሪፖርት ለጉባኤው ተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸውም ማህበሩ በአመቱ ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የሁለገብ ህንፃውን ግንባታ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማስጀመሩና ለግንባታውም የሚውል ሰላሳ ሚሊየን ብር ከከተማ አስተዳደሩ ካዝና ገቢ እንዲሆን ማድረጉ በአመቱ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል እንደሚጠቀስ ገልጸው ከክፍለ ከተማ ጀምሮ በየደረጃው የማህበሩ የመዋጮ ገቢ ወቅቱን ጠብቆ አለመምጣቱ ማህበሩ ስራውን በሚፈለገው ደረጃ ለመስራት አዳጋች እንደሆነበት አስረድተዋል።

በጉባኤው የማህበሩ አባላትና አመራሮች በፕሬዘዳንቱ በቀረበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የተለያዩ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበው በማህበሩ ስራ አስፈጻሚዎች ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን ማህበሩ አብረውት በጋራ ሲሰሩ ለቆዩ አካላት ሽልማት የሚሰጥበትና  በቀጣይ አራት አመታት ማህበሩን የሚመሩ አመራሮች ምርጫም በጉባኤው እንደሚካሄድ ከወጣው ፕሮግራም ለማወቅ ተችሏል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry