7ኛው ከተማ አቀፍ የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በዛሬው እለት በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በድምቀት ተጀመረ።

የዘንድሮው ውድድር የተጠናከረ የመምህራን ህብረት ለከተማችን ሰላምና ለትምህርት ጥራት በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል ።

በመምህራን መካከል የሚካሄድ የስፖርት ውድድር የርስ በርስ ትውውቅን ከማጠናከሩ ባሻገር መምህራን በሚወዳደሩባቸው የስፖርት አይነቶች እምቅ አቅማቸውን እንዲያሳዩ የሚያደርግ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመምህራን ጤና ተጠብቆ አእምሯዊና አካላዊ ብቃታቸው ልቆ በሙያቸው ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ  ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን  አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው በትምህርት ሴክተሩ የሚካሄድ ስፖርታዊ ቢሮው ትኩረት ሰጥቶ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱና ተተኪ ስፖርተኞች ከሚገኙባቸው ውድድሮች መካከል ዋነኛው መሆኑን ጠቁመው ዘንድሮ በመምህራን መካከል የሚካሄደው ውድድር  የተሳካ እንዲሆን ቢሮው ከመወዳደሪያ ሜዳ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራቱን ገልጸዋል።

ውድድሩ ለሁለት ሳምንት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች በተውጣጡ መምህራን መካከል በእግር ኳስ፣ቮሊቦል ፣ጠረጴዛ ቴኒስ እና በቼዝ በተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪይ ስፍራዎች በሁለቱም ጾታዎች የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች መካከል በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተካሄደ የወንዶች እግር ኳስ ጫወታ በይፋ ተጀምሯል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185