ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች

መነሻ ገጽ E የቢሮዉ አስተዳደር E ራዕይ ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ

በአዲስ አበባ ከተማ ውጤታማ የትምህርት ሥርዓት በማስፈን በ2023 ዓ.ም ዓለምዓቀፋዊ ተወዳዳሪ የሆኑ የትምህርት ተቋማትና በልማት’በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ የተሟላ ስብዕና ያላቸው ዜጎች ማፍራት፡፡

ተልዕኮ

የአዲስ አበባ ከተማን ነዋሪ በትምህርት ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ ለትምህርት መዋቅሩ አካላትና በትምህርት መስክ ለተሰማሩ ባለሐብቶች ሞያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት፤ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር የትምህርት ተቋማትን በፍትሐዊነት በማስፋፋት የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ አለምአቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት በተስማሚ ፕሮግራሞች ለህብረተሰቡ ማድረስ፡፡

እሴቶች

  1. ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን
  2. በመልካም ሥነምግባር የታነፁ ዜጎችን እናፈራለን
  3. ፈጠራና ችግር ፈቺነትን እናበረታታለን
  4. በጥናት ምርምር የትምህርት ችግሮቻችንን እንፈታለን
  5. በእውቀትና በእምነት እንሰራለን
  6. ግልፅነት
  7. ተጠያቂነት
  8. ለለውጥ ዝግጁ ነን
  9. የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን
  10. በጋራ መስራት መገለጫችን ነው