ጳግሜ 1የአገልግሎት ቀን ተከበረ ::

by | ዜና

አዲስ አበባ 1/13/2015 ዓ.ም  ጳግሜ 1 የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የኮንስትራክሽን ግንባታና ዲዛይን ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ከሌላው ግዜ በተሻለ ደንበኞችን ለማገልገል ቃል ገብተዋል ::

እለቱን በማስመልከት የኮንስትራክሽን ግንባታና ዲዛይን ቢሮ ኃላፊ ወ /ሮ አያልነሽ ሀብተማርያም ባስተላለፉት መልእክት ሁሉም ሰራተኛ በተመደበበት የስራ ዘርፍ ሀገርና ወገኑን ለማገልገል ከሌላው ጊዜ በተሻለ መነሳሳት በትህትናና በአገልጋይነት ስሜት ስራውን መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል አገልጋይነት በተግባር የሚገለጽ በመሆኑ ሁሉም አካል ጳጉሜ 1ን ሳከብር  በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች በታማኝነት  ለማገልገል ቃል በመግባት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ረጅም ዓመት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ 9 የቀድሞ የስራ ባልደረቦች የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ ስለነበራቸው አገልግሎት ዘመን በማመስገን የምስጋና ሰርተፍኬት መስጠትና የጋቢ ማልበስ ስነስርዓት ተከናውኗል : በጡረታ ላይ ያሉ የቀድሞ ስራ ባልደረቦችም ቢሮው አስታውሶ ላደረገላቸው ሽልማት ምስጋና አቅርበዋል ::

የቢሮው ሰራተኞችም በአዲሱ ዓመት በአዲስ የስራ መንፈስ የባለጉዳዮችን ጥያቄ ለማስተናገድ ቃል ገብተዋል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 311
  • 374
  • 4,292
  • 15,622
  • 98,488
  • 98,488