ጳጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀን ደም በመለገስ ተከበረ

by | ዜና

(አዲስ አበባ 2/13/2015 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮንስትራክሽን ዲዛይንና ግንባታ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ጳጉሜ 2 የመስዋዕትነት ቀንን በማስመልከት የሁለቱም ተቋማት የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኛች ደም ለግሰዋል ::

         

በመስዋዕትነት  ቀን ደም መለገስ ትናንሽ መስዋዕትነትን መለማመድ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ደም ልገሳው በዓመቱ ውስጥ ለሚደረጉ በጎ ሥራዎች መነቃቃት የሚፈጥር ነው ብለዋል :: አቶ አሊ አያይዘውም ደም መለገስ በግንባር ለሚገኙ መከላከያ ሰራዊት አባላት  ፤ በህመም ላይ ለሚገኙና በወሊድ ወቅት በደም መፍሰስ ምክንያት ሕይወታቸውን የሚያጡ እናቶችን ሕይወት ለማዳን ሰፊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አብራርተው የቢሮው ሰራተኞች የመስዋዕትነት ቀንን በማስመልከት የዚህ በጎ አላማ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል ::

በመርሃ-ግብሩ ላይ የሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎችና ሰራተኞች በመገኘት የደም ልገሳ ያደረጉ ሲሆን ዜጎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከተማ አስተዳደሩ ለጳግሜ ቀናት  የተለያየ ስያሜ በመስጠት እየተከበረ እንደሚገኝ የሚታወስ ነው ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 308
  • 374
  • 4,289
  • 15,619
  • 98,485
  • 98,485