ግንባታው እየተፋጠነ በሚገኘው ጄነራል ታደሰ ብሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም) በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንዲሁም የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በከላሌ ጄነራል ኮንስትራክሽን አማካይነት በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሎላ አርኪቴክት የማማከሩን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ በተለይም የመማሪያ ክፍሎችና የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ወደ መጠናቀቅ ደረጃ መድረሱን በምልከታው ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው ከምድረ ግቢው ጋር በተገናኘ እየተሰሩ የሚገኙ የግንባታ ስራዎች በፍጥነት ተጠናቀው ትምህርት ቤቱ  ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ እንዲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮችም የትምህርት ቤቱ ግንባታ በፍጥነት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የግንባታውን ሂደት በቅርበት የሚከታተሉ የተማሪ ወላጅ ተወካዮችም ህብረተሰቡን በማስተባበር ለትምህርት ቤቱ ግንባታ የሚሆን ሀብት የማሰባሰብ ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምልከታው ለተገኙ አካላት ገልጸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 28
  • 222
  • 1,582
  • 6,362
  • 214,623
  • 214,623