(አዲስ አበባ 6/2/2016 ዓ.ም) ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢትዬጵያ ኢንዱስትርያል ግብአቶች ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ያደረገ ሲሆን ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወይንሸት ዘሪሁን ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስረክበዋል፡፡
የንጽህና መጠበቂያዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የሚውል መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያ ወይዘሮ ትግስት በሪሁን አስታውቀዋል፡፡
ባለሙያዋ አክለውም በዛሬው እለት ቢሮው ግምታቸው 4.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ 71,485 የንጽህና መጠበቂያዎችን መረከቡን ገልጸው ድጋፉ በንጽህና መጠበቂያ ችግር ምክንያት ሴት ተማሪዎች ላይ የሚከሰተውን መጠነ ማቃረጥም ሆነ መድገም እንደሚቀርፍ አስገንዝበዋል፡፡
በርክክቡ የተገኙ ተማሪዎችም ድጋፉ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የኢትዬጵያ ኢንዱስትርያል ግብአቶች ልማት ድርጅት ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
0 Comments