ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 27/2016 ዓ.ም )  በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣የጉለሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራ እና የወረዳ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

አመራሮቹ ምልከታ ካደረጉባቸው ተቋማት መካከል አንዱ እንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን በትምህርት ቤቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ቤቱ አመራሮች ከተማሪና ወላጅ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር የመማር ማስተማር ስራው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸው የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮችም በትምህርት ቤቱ የሚያደርጉትን ድጋፍና ክትትል አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር በስሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸው ያለምንም እንከን እንዲከናወን ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622