(መስከረም 18/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሀይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከቢሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያልተመዘኑና የስራ ዝርዝር ያልተቀመጠላቸውን መደቦች ለማስተካከል የሚያስችል ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስራውን እንዲሰራ ለተቋቋው ኮሚቴ መስጠቱን አሳውቋል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰው ሀይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሀኑ ከበበው የሚቀረጹ የስራ ዝርዝሮች በማዕከል 39 ፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ 9 እና በወረዳ ደረጃ 2 መሆናቸውን በመግለጽ እነዚህ ስራዎች እንዲመዘኑ ለማድረግ እዲቻል ለተቋቋመው ኮሚቴ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
0 Comments