የ2017 ዓ.ም የግማሽ አመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ተደረገ፡፡

by | ዜና

(ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈትቤቶች የተካሄደ ሲሆን በትላንትናው እለት በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት አማካይነት ድጋፍና ክትትሉን ለሚያካሂዱ ባለሙያዎች በተዘጋጀው መስፈርት ዙሪያ ኦረንቴሽን መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ የጽህፈት ቤቶቹን የግማሽ አመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የቢሮው የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ፋንታሁን እያዩ ከስራ ክፍሉ ባለሙያ አቶ ግዛቸው ጋር በመሆን የድጋፍና ክትትል ሂደቱን በትምህርት ጽህፈት ቤቶቹ በመገኘት ተመልክተዋል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት ያለምንም እንከን መካሄዱን ከትምህርት ጽህፈት ቤቶች እና ድጋፉን ካደረጉ ባለሙያዎች ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ፋንታሁን እያዩ አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይ በሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት አማካይነት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የአንደኛ መንፈቅ አመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ምዘና የሚካሄድ መሆኑ ተገልጻል፡፡

0 Comments