(ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ መረጃ ዳይሬክቶሬት የ12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስመልክቶ በክፍለ ከተማ ለሚገኙ የትምህርት ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና ለቢሮው የአይሲቲ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡
በኦረንቴሽኑ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ያሉ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችና የኔትወርክ ዝርጋታ ያለበት ሁኔታ በቀጣይ በመመልከት ፈተናውን በበቂ አቅምና ቅንጅት ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እንደሚደረግ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን በመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በኦንላይን ለመስጠት እቅድ መያዙን አብራርተዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ቀደም ሲል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን እየተጠቀሙ ያሉ ቢሆንም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ አቅም እንዳላቸው ማየት ተገቢ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ የኦንላይን ፈተናውን በአግባቡ ለመስጠት መሰረተ ልማቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅና በመረጃ የተደገፈ ማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
0 Comments