የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነውና ቂርቆስ ክፍለከተማ በሚገኘው አጼ ቴውድሮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የፈተናው አጀማመርን በተመለከተ ከክፍለከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ምልከታ አድርገዋል።
በቂርቆስ ክፍለከተማ ዘንድሮ በ14 የፈተና ጣቢያዎች 3,865 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በለው ተስፋ ገልጸው 97ፈታኞችና 34 ሱፐር ቫይዘሮች ፈተናውን እንዲያስፈጽሙ መመደባቸውን አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75,100 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ቀደም ሲል መግለጻችን ይታወቃል።
0 Comments