የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሠሌዳ

by | ዜና

ቀን 21 /1/2015 ዓ.ም

የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሠሌዳ

የትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሠሌዳ ይፋ አደረገ።

በዚህ መሠረት በመጀመሪያ ዙር የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ከመስከረም 26 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን÷ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ይሰጣል፡፡

ከመሰከረም 30 እሰከ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ፈተና ይሰጣል፤ ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

በሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

በዚህም ጥቅምት 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ለተፈታኞች ይሰጣል።

ከጥቅምት 8 እሰከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን፥ ከጥቅምት 12 እና 13 ቀን 2015 ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው እንደሚመለሱ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948