የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአብዮት እርምጃ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም) “መቼም ፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካታት ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን ፣ የቂርቆስ ከፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የልዩ ፍላጎትና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ኤርሚያስ አካሉ ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር መ/ሪት ፋሲካ ወርቁ እንዲሁም መምህራን፣ተማሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካተት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን  በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚደረሱ ጾታን መሰረት የደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ብቁና የተሻለ ትውልድ መፍጠር የሁሉም ዜጋ ኃላፍነት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የጥያቀና መልስ ውድድር የተካሄደ  ሲሆን ለአሸናፉ ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመርሀ-ግብሩም ተማሪዎች የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ጭፈራዎችን ፣  የኪነ-ጥበብ ስራዎችን  በመነባንብ ፣ በስነ-ግጥምና በጭውውት አቅርበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625