የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ::

by | ዜና

(ቀን 12/2/2016 ዓ.ም)  የሀገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ የሀገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉን ገልዖ በ2016 ዓ.ም ሀገራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ወስደው 62 (50%) እና በላይ የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል ያገኙ ተፈታኞች ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በዚሁ ደብዳቤ አመልካቾች ለማመልከት ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ http://portal.aau.et/web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን መግቢያ ስም ( user name) እና የይለፍ ቃል (password) ተጠቅመው ማረጋገጥ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475