(አዲስ አበባ 22/1/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለቢሮው የህንጻ አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኞች ሰልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናው የደንበኛ አገልግሎትና የስታንዳርድ ምዝገባ ላይ ትኩረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን የውስጥና የውጪ ደንበኛን እንዴት ማገልገል እንደሚቻል፤ስራዎችን በእቅድ በመምራት መፈጸም የሚረዱ ዘዴዎችና ስራን በቡድን ለማከናወን የሚያግዙ ነጥቦች በዋናነት ተዳሰዋል፡፡
የለውጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ዳዊት ከበደ የመንግስት ሰራተኛ ህዝብን የማገልገል ሃላፊነትን የተሸከመ እንደመሆኑ መጠን የግልና የተቋም ለውጥን ለማምጣት ህግና ደንብን በማስተግበርና የህብረተሰብ ደህንነትን በመጠበቅ ስራውን ማከናወን እንደሚገባ ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት አብራርተዋል፡፡አቶ ዳዊት አያይዘውም የፐብሊክ ሰርቪስ ስራ ውጤታማ እንዲሆን በተቀናጀ መልኩ ስራዎችን ማከናወን ከሁሉም ሰራተኞች እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
የህንጻ አስተዳደር ሰራተኞችም በሙያዊ ስነ-ምግባርና የተለየ ጥንቃቄ ደንበኞችን ማገልገልና ያላቸውን የስነ-ምግባር ልህቀት በስራቸው እንዲያሳዩና የተጣለባቸውን ሃላፊነትም በቡድን ስሜትና በመግባባት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ሰራተኞች ከስራ ክፍላቸው የወረደ አመታዊ እቅድን በስታንዳርዱ መሰረት የእለት ንጽጽር ለመስራትና ሳምንታዊ ሪፖርት ለማዘጋጀት የሚያስችል ፎርማት ላይ የተግባር ልምምድ አድርገዋል፡፡
ስልጠናው በቀጣይ ዙር ለቀሩ የቢሮ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ከክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments