ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት እንደሚሰጥ አሳውቋል።
የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱም ተገልጿል ።
በ2014 ዓ.ም የህግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉም ተብሏል።