የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የስርዓተ ፆታ ዘርፍ የስርዓተ ፆታ ጥቃትን አስመልክቶ ስልጠና ሰጠ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 23/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የስርዓተ ፆታ ዘርፍ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችን መከላከል አላማው ያደረገ ስልጠና ሰጥቷል ::

በስልጠናው ትምህርት ቤቶች ከጥቃት የፀዱና ፆታን በተመለከተ ጥቃት የማይደርስባቸው ፤ ሕፃናት በሰላም የሚማሩባቸው ምቹ ቦታ እንዲሆኑ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ስልጠናውን የሰጡት የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ሳምራዊት አማረ አሳስበዋል ::

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚደርሱ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መከላከል ብቁና የተሻለ ትውልድ ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል  ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ፆታ ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን በስልጠናው የሚሳተፉ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንና የስርዓተ ፆታ ተጠሪ ባለሞያዎች ከሌላው በተለየ የፆታዊ ጥቃትን የመከላከልና ሕጎችን ማስተማር እንደሚገባቸው ተናግረዋል ::  አያይዘውም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን የመቃወም ዘመቻ በሁሉም የትምህርት ተቋማት እንዲደረጉ ጠይቀዋል ::

የፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ትምህርት ሚኒስቴርና ዩኒሴፍ በጋራ ያወጡት መመሪያም የትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ሕፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ የወጣቶች ዘርፍ ቡድን መሪ በሆኑት አቶ እስክንድር ላቀው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ::

መመሪያው በ 2016 ትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ፆታዊ ጥቃት ላይ ሰፊ ግንዛቤ በመያዝ ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል እንደሚያስችል የተገለፀ ሲሆን በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችል ከቀላል እስከ ከባድ ቅጣት የሚደርስ ዝርዝር ሃሳብ የያዘ መሆኑ ተነግሯል ::

በተያያዘም ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 11 የሚካሄደው የዘንድሮው የፀረ ፆታ ጥቃት ቀን “መቼም የትም በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃት ይቁም እንበል! ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ ከስራ ዘርፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 2
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625