ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንየዕቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ልማት ዳይሬክቶሬት

የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት

  1. የዕቅድና በጀት ዝግጅት

1.1. የስራ ሂደቱን ዕቅድ ማዘጋጀት፣

1.2   በተቋሙ ስር ካሉ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ከስራ ሂደቶች የተቋሙን  የተጠቃለለ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣

1.3  የተቋሙን የአጭርና መካከለኛ ጊዜ ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት፣

1.4. ለተቋሙ ተጠሪ የሆኑ ጽ/ቤቶች/ የስራ  ሂደቶችን ዕቅድና በጀት መከታተልና መደገፍ እንዲሁም እንዲናበብ ማድረግ፣

1.5. በዕቅድና በጀት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት፡፡

 2.የበጀት ማዘዋወር ስራዎች

2.1. የበጀት ዝውውር ማስፈፀምና መከታትል

2.2. ተጨማሪ በጀት መጠየቅና ማስፈቀድ፣

2.3. የበጀት አጠቃቀም ክትትል ማድረግ፣

2.4. የበጀት መመሪያዎችና ኖርሞችን ተፈፃሚነት ማረጋገጥ፡፡

 3.የዘርፍ ጥናት ማካሄድ

3.1. በተቋሙ ውስጥ ያሉትን ቁልፍ ችግሮች መለየት፣

3.2. TOR/ ዝክረተግባር/ ማዘጋጀትና ለበላይ አመራር አቅርቦ ማፀደቅ፣

3.3. አሳታፊና ችግር ፈቺ ጥናቶችን ማካሄድ፣

3.4. ውጤታማነታቸውን ወይም ተግባራዊነታቸውን መታተል፣

  1. የአፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ ማድረግ

4.1. ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፣

4.2. በተቋሙና በስሩ በሚገኙ መ/ቤቶች በቼክ ሊስቱ መሰረት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

4.3. ከክትትልና ግምገማ የተገኘውን ውጤት ለበላይ አመራር ማቅረብ፣

4.4. በተገኘው ውጤት መሰረት ግብረ መልስ መስጠት፣

4.5. ወርሃዊ/የሩብ ዓመት/ዓመታዊ ሪፖርት ማዘጋጀት፣ማሰባሰብ ፣ማጠናቀርና ማሰራጨት፣

  1. የልማት ፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ ማካሄድ

5.1. ቼክ ሊስት ማዘጋጀት፣

5.2. በተቋሙና በስሩ በሚገኙ መ/ቤቶች የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣

5.3. ከክትትልና ግምገማ የተገኘውን ውጤት ለበላይ አመራር ማቅረብ

5.4. በተገኘው ውጤት መሰረት ግብረ መልስ መስጠት፣

  1. መረጃዎችን ማሰባሰብና ማደራጀት

6.1. የሚሰበሰቡ መረጃዎችን መለየት፣

6.2. መረጃ ማሰባሰቢያ ቅጾችን ማዘጋጀት፣

6.3. መረጃዎችን በአግባቡ ማደራጀትና ለተጠቃሚ ዝግጁ ማድረግ፣

  1. የእርዳታና ብድር ፕሮጀክቶች ዝግጅት

7.1.ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ማዘጋጀት፣

7.2. ለበላይ አመራረር   ማቅረብና ማፀደቅ

7.3. ፈንድ ማፈላለግ፣

7.4. ተግባራዊነቱን መከታተል፣

    8.የሪሶርስ ሞቢላይዜሽን ስራዎችን መስራት

8.1. የሪሶርስ እጥረትና ትርፍ ያለበትን መለየት፣

8.2. ትርፍ ሪሶርስ ካለበት ወደሌለበት የሚዞርበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

8.3. ተግባራዊነቱን መከታተልና ለበላይ አመራሩ ማሳወቅ፣