የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጠ ::

by | ዜና

(ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም)  የእቴጌ መነን  የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በ 2015 ዓ. ም የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ላለፉ ተማሪዎች የእውቅናና ሽኝት መርሃ ግብር አካሂደዋል ::

የእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ወ /ሮ ሃና ፀጋዬ  ለተማሪዎች መምህራንና ወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የእውቅና መድረኩ መዘጋጀትም በ2016 ሀገር አቀፍ ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎች ልምድ ለማካፈል እንደሚጠቅምና ትምህርት ቤቱም በ 2016 ዓ. ም ሁሉንም ተማሪ በከፍተኛ ውጤት ለማሳለፍ በቂ ዝግጅት ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል ::

ወ /ሮ ሃና ተማሪዎች ከአንዱ የሕይወት ምእራፍ ወደቀጣዩ የሕይወት ምእራፍ መሸጋገራቸው ሳያዘናጋቸው በዚህ ትምህርት ቤት ያሳዩ የነበረውን ስነ-ምግባር ይዘው በዩኒቨርስቲ በሚገጥማችው ፈተና እየፀኑ ኢትዮጵያን የሚረከቡ ሴቶች መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል :: አያይዘውም በአራት ዓመት የትምህርት ቤቱ ቆይታቸው ላሳዩት መልካም ስነ-ምግባር እና ላገኙት ከፍተኛ ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መምህራንና ወላጆችም ለተገኝው ስኬት የነበራቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዉ ሲያደርጉ ለነበረው ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበዋል ::

በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ በ 2015 ዓ. ም የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በ2016 ዓ. ም የ 12 ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል::

ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሁሉም ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት እና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም ለቀጣይ ትምህርታቸው የሚያግዙ ቁሳቁሶች በስጦታ ተበርክቶላቸዋል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948