ቀን 25/9/ 2014 ዓ.ም
የኢትዮ ቴሌኮም ያቋቋማቸዉን የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት (Digital Learning Centers) አስመረቀ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ያቋቋማቸዉን የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት (Digital Learning Centers) በዛሬዉ ዕለት በከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አስመረቀ፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ብሎም የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጎችን በዕውቀት ለማነጽ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በኢትዮጵያ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ከሚከናወኑ በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል በተለያዩ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ45.48 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተቋሙ ያቋቋማቸዉን 66 የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት (Digital Learning Centers) ተጠቃሽ ሲሆኑ በዛሬው እለት ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡
Bridging Divide Digital Center የተባለው ፕሮጀክቱ፤ 140 ሺህ 596 ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
ትምህርት ቤቶቹ የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት እና የትምህርት መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈፃሚተናግረዋል፡፡
0 Comments