(ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም) ስልጠናው ለክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስተባባሪዎች እና በክፍለከተማ ደረጃ ለተቃቃመው የጥናትና ምርምር ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም በጥናትና ምርምር አሰራርና አስፈላጊነትን መሰረት አድርጎ መሰጠቱን ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሀንስ ተስፋዬ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት አዲስ የተደራጀ የስራ ክፍል እንደመሆኑ በዳይሬክቶሬቱ ከሚከናወኑ ተግባራት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያግዝ መርሀ ግብር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ቢሮው በ2017 ዓ.ም ስትራቴጂ ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገበት የሚገኘውን የተማሪዎችን የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት የማሻሻል ተግባር በጥናትና ምርምር የተደገፈ እንዲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ እንዲሰሩ የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን ጠቁመው በየትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን የላቀ ለማድረግ ውጤታማ የማስተማሪያ ስነ ዘዴ የሚተገብሩ መምህራንን ልምድ ወደ ሌሎች ማስፋፋት እንዲቻል የሚያግዝ ስልጠና መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የአጠቃላይ ትምህርት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ስልጠና ሰጠ፡፡
0 Comments