የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በትላንትናው እለት የጀመረው የሞጁል ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

by | ዜና

(ጥር 25/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ የመረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪዎችን ጨምሮ ከቢሮው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ከአመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት አዘገጃጀት እና ከአጠቃላይ ትምህርት አመላካቾች ጋር በተገናኘ በትላንትናው እለት የተሰሩ የአርትኦት ስራዎች ተገምግመዋል።


በተያያዘ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ለመ ሰብሰብ በሚያግዙ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች እና በትምህርት ሚኒስቴር በበለጸገው stat educ2-2017 ሶፍትዌር ዙሪያ በዳይሬክቶሬቱ አማካይነት ስልጠና ተሰቷል።

0 Comments