(መስከረም 10/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት መሰከረም 6/ 2017 ዓ.ም መጀመሩን ተከትሎ የትምህርት አጀማመሩን አስመልከቶ ግምገማ ተካሂዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቢሮ ሀላፊ ተወካይ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት በከተማ አስተዳደሩ በድምቀት መጀመሩን በመጥቀስ አጀማመሩን አስመልክቶ በተካሄደ የሱፕርቭዥን ግኝት ላይ እና አጀማመሩን በተመለከተ በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች የቀረበዉን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ግምገማ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡
ሀላፊዋ አክለዉም ከቀረቡት ሪፖርቶች በመነሳት በትምህርት አጀማመሩ ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና እጥረቶችን በማስተካከል የመማር መስተማር ስራዉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከተማሪዎች አቀባበል ወጥቶ በክፍል ውስጥ የመማር መስተማር ስራዉ ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በግምገማዉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቢሮ ሀላፊ ተወካይ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
0 Comments