የአዲስ አበባ ከተማ አ ተዳደር ትምህርት ቢሮ ዓለም አቀፉን የፀረ ሙስና ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይት አካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም) የዘንድሮ የጸረ ሙስና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ እንዲሁም በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤በሕብረት እንታገል በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የፀረ ሙስና ትግሉ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችለው ሁሉም ባለድርሻ አካል ተግባሩን በአግባቡ መታገል ሲችል እንደመሆኑ የትምህርት ማህበረሰቡ በፀረ ሙስና ትግሉ ተሳታፊ በመሆን የትውልድ  ሥነ ምግባር ግንባታው ውጤታማ እንዲሆን ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የቢሮው ሰራተኞች ለውይይት በቀረበው  ሰነድ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆንበዋናነትም ሙስና መከላከል የሚቻለው በየደረጃው የተጠያቂነት ስርአት ማስፈን ሲቻል መሆኑን በመጠቆም በትምህርት ዘርፉ ተግባሩ ውጤታማ እንዲሆን ዘንድሮ የተጀመረውን የግብረ ገብ ትምህርት በአግባቡ መስጠትና በትምህርት ቤቶች የሚገኙ ክበባትን መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የቢሮው አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ሙስና የሀገርን ኢኮኖሚ የሚያዳክምና የዜጎችን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያ ሳጣ ተግባር በመሆኑ ተግባሩን ሁሉም ሊታገለው እንደሚገባ ጠቅሰው የትምህርት ተቋማት በፀረ ሙስና ትግሉ ግንባር ቀደም በመሆን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 26
  • 222
  • 1,580
  • 6,360
  • 214,621
  • 214,621