የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 24/ 2016 ዓ.ም)  በመርሃ-ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እንኳን አደረሳችሁ በማለት ቢሮ  በዓላት በመጡ ቁጥር ያሚያካሂደው የማዕድ መጋራት መርሀ-ግብር የቢሮ አንዱ ባህልና የብሮነትና የአንድነት  ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን አክለውም በጎነትን በማስፋፋት ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት ተጨባጭ ውጤት እየታየበት መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብሩ ላይ 230 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በቦታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊን ጨምሮ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

                                 

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948