የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ለክፍለከተማና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ለሁለት ቀን የሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 22/ 2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት ከአዲሱ ስርአተ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ የመምህራን እለታዊና አመታዊ እቅድ አዘገጃጀት ፤ በሱፐርቪዥን ጽንሰ ሀሳብና በአፈጻጸም ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የተከታታይ ምዘና ሂደት እና(continus assessment) እና ተግባራዊ ጥናትን (action research) መሰረት አድርጎ በቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ነው የተሰጠው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የመምህራንንም ሆነ ርዕሳነ መምህራንን አቅም እየገነቡ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ሱፐርቫይዘሮቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ እውቀትና ብቃትን ታሳቢ ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው የክፍለከታ እና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች በትምህርትቤቶች ድጋፍና ክትትል በሚያደርጉበት ወቅት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎች ዙሪያ በቡድን እና በጋራ ባደረጉት ውይይት በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ጠቁመው በቀጣይ በትምህርት ቤቶች ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በአፈጻጸም የሚታዩ ልዩነቶችን በማቀራረብ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሱፐርቪዝን ስራ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ በየደረጃው ለሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዬ አሰፋ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957