የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ስርአቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት ለመቅረፍ የሚያስችል ውይይት አጠቃላይ ሰራተኛው በተገኘበት አካሄደ፡፡

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 8/ 2016 ዓ.ም) ጥናቱ በዋናነት በትምህርት ልማት ስራው እያጋጠሙ የሚገኙ ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በማጥናት በጥናቶቹ ግኝቶች መሰረት ችግሮቹን በመቅረፍ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ታስቦ የሚካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ገልጸው ቀደም ቢሎ የቢሮው የማኔጅመንትና የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ጥናቱ በሚደረግባቸው ርእሰ ጉዳዮችና አስፈላጊነት ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ጥናቱን እንዲያደርጉ የተመረጡ የትምህርት ባለሙያዎችን እና አመራሮችን እንዲሁም ጥናቱ የሚካሄድባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች አቅርበው ውይይት የተካሄደ ሲሆን ጥናቱን እንዲያካሂዱ የተመደቡ የኮሚቴ አባላትም የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ተረድተው በአስቸኩዋይ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተሰቱዋል፡፡

                           

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 184
  • 249
  • 2,420
  • 8,972
  • 243,954
  • 243,954