የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጫወታን መሰረት ባደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ ዙሪያ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት መምህራን የሚ ሰጠው ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

by | ዜና

(ቀን ጥር 29/2016 ዓ.ም) ስልጠናው ከግል ትምህርት ቤት ለተውጣጡና ቀደም ሲል ስልጠናውን ላልወሰዱ መምህራን የተሰጠ ሲሆን ቀደም ሲል የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠናው መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ስልጠናው መምህራኑ ተማሪዎቻቸውን ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ተከትለው  ማስተማር እንዲችሉ በተግባር ተደግፎ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው ገልጸው በቀጣይ የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ከዚህ በፊት ስልጠና ላልወሰዱ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622